ዛሬ በወጣትንት ዘመናችን በምንወስናቸው ውሳኔዎች የነገ ህይወታችንን ቅርፅ ማስያዝ እንችላለን ብዮ አምናለሁ፡፡ ከነዚህ ውሳኔ የሚፈልጉ ነገሮች መካከል ደግሞ ወሲብና ተዛማጅ የጤና ጉዳዮች ወሳኝ እንደሆኑ ይሰማኛል፡፡ እኛ ወጣቶች በምድጃችን ላይ ብዙ ድስቶች የጣድን ቢሆንም እነደሌሎቹ ድስቶቻችን ሁሉ፣ወሲብና ተዛማጅ የጤና ጉዳዮቻችን ትልቅ ትኩረት ልንሰጣቸው ይገባል፡፡ በተለይ በዙሪያችን የሚከናወኑትን እውነቶች ስናይና አንዳንድ ጥናቶች የሚያወጡትን ሪፖርቶች ስንመለከት ጉዳዩ አሳሳቢ እንደሆነ ለመረዳት አያዳግተንም፡፡
ወሲብና ተዛማጅ የጤና ጉዳዮቻችንን በጥንቃቄና መረጃ ላይ በተመሰረተ ውሳኔ መምራታችን ጤናማ ሰውነትን፣ ከስጋት የነጻ ወሲባዊ ህይወትን፣ አወንታዊ የፍቅር ግንኙነትንና የአዕምሮ ሰላም የተሞላ አስደሳች ዘመንን ለመምራት ያስችለናል፡፡ ለዚህም በመጀመሪያ ራሳችንን ማክበር በመቀጠል ደግሞ ለእኛ ትክክል የሆነውን ነገር በሌሎች ግፊትና ምርጫ ሳይሆን በራሳችን ሚዛን ለክተን መምረጥ መቻል ይኖርብናል፡፡
ወሲብ ተፈጥሯዊ የሆነ የህይወት ክፍል ሲሆን በጥንቃቄና በአግባቡ ከተመራ ለህይወታችን ዕርካታን፣ቅርርቦሽንና ደስታን ሊያጎናጽፋት ይችላል፡፡ መቼ፣ የት፣እንዴትና ከማን ጋር ልፈጽመው የሚለው ውሳኔ ግን የግላችን ነው የሚሆነው፡፡ በህይወታችን የምናደርገውን ነገር የመምረጥ ነጻነት ያለንን ያህል ምርጫችን የሚያስከትለው ውጤት በቀጥታ በቀደመው ውሳኔያችን ስለሚወሰን ውጤቱን የመምረጥ ነጻነት የለንም፡፡ ለዚህ ነው መጀመሪያ ላይ መጠንቀቅ ያለብን፡፡ ስለሆነም የምንፈልገውን ነገር ከራሳችን ግላዊ እሴት፣ ውስጣዊ መሻትና ወሰን/ድንበር አንጻር አመዛዝንን መወሰን አለብን፡፡ እዚህ ላይ የፍቅር ጓደኛሞች እርስ በእርሳቸው ሊከባበሩ፣ ሊጠባበቁና አንዳቸው ለአንዳቸው ምቾት የሚሰጡ ሊሆኑ ይገባቸዋል ለማለት እወዳለሁ፡፡ እናንተስ ምን ትላላችው?
- Arsema Germanikos
- Sexual & Reproductive health
- Thursday, 06 April 2017
Comment
There are no comments made yet.
- Page :
- 1
There are no replies made for this post yet.
Be one of the first to reply to this post!
Be one of the first to reply to this post!