ወጣቶች በሕይወታቸው ሁለት ምዕራፎች ላይ ለኤች አይ ቪ የተጋለጡ ናቸው፡፡ በሕይወት የመጀመሪያዎቹ አሥር ዓመታት ኤች አይ ቪ ከእናት-ወደ-ልጅ ሊተላለፍ ይችላል፣ በሕይወት ሁለተኛው አስርት ዓመታት በጉርምስና ዕድሜ ላይ ለኤች አይ ቪ አዲስ ተጋላጭነት ይመጣል፡፡ እነዚህን በመጠኑ እንመልከታቸው፡፡
በሕይወት የመጀመሪያዎቹ አሥር ዓመታት ውስጥ ፡በ 2013, በግምት 240,000 ሕፃናት በእርግዝና, በወሊድ ወይም ጡት በማጥባት ጊዜ በእናታቸው ምክንያት በኤች አይ ቪ ተጠቅተው ነበር፡፡ ከነዚህ ልጆች ብዙዎቹ ሕፃናት ለቫይረሱ የተጋለጡበት ምክንያት ከእንክብካቤ ጋር የተገናኘ ነበር፡፡ ይህ በጉርምስና ዕድሜ ከሚከሰቱ ተጽዕኖዎች፣ አዳዲስ ኃላፊነትቶችና አንዳንድ አደገኛ ባህሪያት ጋር ተዳምሮ የኤችአይቪ ሕክምና ፍላጎትንና እና የወጣቶችን ጤንነት የማስጠበቅ ስራን አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡
በሕይወት ሁለተኛው አስርት ዓመታት ውስጥ፡ ጥንቃቄ የጎደለው ወሲብ በቀዳሚነት የተበከለ መርፌ በጋር መጠቀም በሁለተኛነት, በዚህ የህይወት ምዕራፍ ለወጣቶች የኤች አይ ቪ ተጋላጭነት ዋና ምክንያቶች ናቸው፡፡ ጥንቃቄ በጎደለው ወሲብ በኩል ተጋላጭነት ስንል በለጋ ዕድሜ የወሲብ ግንኙነት መጀመርን፣ ኮንዶምን ሁልግዜና በአግባቡ አለመጠቀምን፣ ከበርካታ (ከአንድ በላይ) ሰዎች ጋር የወሲብ አጋርነት መመስረትንና በዕድሜ ከሚበልጡን (በዕድሜ ከገፉ) ሰዎች ጋር የወሲብ ግንኙነት መፈፀምን ያጠቃልላል፡፡
ለመሆኑ ለምንድነው እነዚህ ምክንያቶች ወጣቶችን ለኤች አይ ቪ ተጋላጭ የሚያደርጎቸው? ሀሳብዎን ያጋሩን!
- Dr TemariNet DKT
- Sexual & Reproductive health
- Friday, 19 August 2016
Comment
There are no comments made yet.
- Page :
- 1
There are no replies made for this post yet.
Be one of the first to reply to this post!
Be one of the first to reply to this post!