- Hiwot Berhanu
- Love and Relationship
- Friday, 08 March 2019
ስሜ ባንቺአምላክ ይባላል፤ ፍረሽ የካምፓስ ተማሪ ነኝ፣እንደ ጊቢ ተማሪ ብዙም ሳልፍታታ ብዙም ሳልጨናነቅ ያመንኩበትን እና ለልቤ ያስደሰተውን እያረኩ የምኖር ወጣት ነኝ፡፡ ፍቅረኛ አለኝ የፍቅር ዳር ዳሩን የጀመርነው ገና ወደ ዩኒቨርስቲ ሳንመጣ ፕሪፓራቶሪ እያለን ነው፡፡ ጸጋው ይባላል አስተወይ እና ተናፋቂ ጉብል ነው፤ ጊቢ ከመጣን በኋላ ቅርርባችን እየጨመረ እና እየተላመድን መጥተናል፤ የቤተሰቦቻችንን ተስፋ እና የነገ ህይወታችንን ለማቃናት ለትምህርታችን ትኩረት እንሰጣለን ግሬድ እንዳናበላሽ ተጠንቅቀን ቸክለን ጥሩ ውጤት በማምጣት ላይ ነን፡፡ በቀን ውስጥ ብዙ ሰዓታትን አብረን እያሳለፍን ነው እሱ ከዶርም ሜቶቹ እና ከጓደኞቹ የሚሰማው ነገር እና የሚደርስበት የአቻ ግፊት ከተስማማንበት ሀሳብ እንዲያፈነግጥ አርጎታል በተደጋጋሚ ለsex ይገፋፋኛል፤ አንዳዴም "ለምን sex አናረግም?'' ብሎ ይጠይቀኛል የተነጋገርነውን ደግሜ እነግረዋለሁ፤ ባረግዝስ ብዬ እለዋለሁ:: ''ኮንዶም መጠቀም እንችላለን'' ይላል:: እኔ ግን ምንም አልዋጥልሽ ብሎኛል፤ እንዳውም ለ sex ፈታ ያሉ ናቸው ከሚባሉ ሴቶች ጋር ከበፊቱ በላይ ሲቀራረብ እያየሁ እየፈራሁ ነው፡፡ ጸጊን ባጣ ምንድን ነው የምሆነው? እሱን ከማጣ ባላምንበትም ወሲብ ልፈጽም ወይስ በአቋሜ ጸንቼ ልኑር እያልኩ ሳሰላስል ከርሜ በእምነቴ ለመጸናት ወስኛለሁ። መታቀብ የኔ የህይወት ውሳኔ ነው፡፡ ፍቅረኛ ያላት የካምፓስ ሴት መታቀብ አትችልም??????
Comment
There are no comments made yet.
There are no replies made for this post yet.
Be one of the first to reply to this post!
Be one of the first to reply to this post!