1. Hiwot
  2. Love and Relationship
  3. Sunday, 24 March 2019
መቼም ጊቢ ውስጥ የማይወራ ነገር የለም፤ ስለ ሁሉም ነገር ይወራል በተለይ በዳርም ሜቶች መሀል መግባባት ስር ሲሰድ ወሬ፣ ሀሜት፣ ፍቅር፣ ናፍቆት ብቻምን አለፋችሁ e.tng ይወርል።
የሰሞኑ የጊቢያችን issue ደግሞ 5ቱ ጓደኛማቾች ናቸው፤ስፖርተኛው ሰውነታቸው፣ ቁመናችው፣ስታይላቸው የደስ ደሳቸው ሙዳቸው በጣም ደስ ይላል፤ዶርም፣ካፌ፣ቡና ተራ ላይብረሪ ሁሉም ጋር የነሱ ነገር ይነሳል ስለ እነሱ አለማውራት ቢቻል እንኳን አለመስማት ግን አይቻልም፤ከዳኒ ጋር አንድ ዲፖርትመንት አንድ ክላስ ነን፤ ለአመታት እብረን ስንማር በዚህ መልኩ አይቼውም ሆነ አስቤው አላውቅም ነበር፤ሳላውቀው ስለ ግሩፑ አባል ስለ ዳኒ መስማት እየሳበኝ መቶል ስለሌሎቹ ሲወራ ግድ የማይሰጠው ጃሮዬ ስለሱ ሲነሳ ይቆማል ሳየው መርበትበት ጀምሬአለሁ፤ ስለዚህ ስሜት ጓደኞቼም ሆኑ የዳርም ሜቶቼ እንዲያውቁ አልፈልግም ነበር ግን በተለያየ ጊዜ ባልታሰበ ሁኔታ ስለሱ ለማወቅ በመጒዋገውት የምጠይቀው ጥያቄ የጓደኞቼን አቴንሽን እንድስብ አድርጎኛል ፍርዬ እንቺ ልጅ ምንድነው interview ማብዛት ብላ ስታልፈኝ መጀመሪያ ሁኔታዬን አይታ ስሜቴ የገባት ነፂ ግን እርፍ እንደዚህ ነው ጆፌ መጣል ብላ በተሰበሰብንበት እውነቱን ስታፈነዳው ምን ያህል ቀልቤ እንደተገፈፈ እኔ ነኝ የማውቀው፤ ይህን የኔን ስሜት ካወቁ በኃላ ሁሉም በተለያየ ጊዜና ቦታ ለምን ፍቅርሽን አትነግሪውም ይላሉ፤ አንዳንዴ ደግሞ ተንክርፍፌ ለሌላ ሴት አሳልፌ እንዳልሰጠው ያስጠነቅቁኛል፤ በርግጥ እነሱም ልክ ናቸው ዳኒን ሳላይ መዋል እያቃተኝ ነው ግን ደግሞ እኔ እሱን በዚህ መልኩ ያሰብኩት አሁን ነው ሁሉም ሲይወሩለት ነው፤ እሺ ፍቅሬን ልንገረው ብልስ እንዴት ነው የምነግረው? ምንስ ብዬ ነው የማናግረው በዛላይ ከዚህ ሁሉ የጊቢ ሴት መሀል እኔን እንዴት ይመርጣል? ግን እሱን መውደዴ በራሱ ትክክል ነው? ምን ጋር እንደሆንኩ እንኳን አላቅም በትክክል ፍቅር ውስጥ ወይስ በስሜት ቁጥጥር ውስጥ? am confused
Comment
There are no comments made yet.


There are no replies made for this post yet.
Be one of the first to reply to this post!