1. Rita Mane Ayallew
  2. Life Skills
  3. Tuesday, 16 February 2016
በጫት ተክል ወይም ቅጠል ውሰጥ ብዙ የሆኑ ንጥረነግሮች (ኪሚካሎች) ሲኖሩ፤ በጤንነት ላይ ጉዳት ያሰከትላሉ ተብለው በይበልጥ የሚታመንባቸው ሶሰት ናቸው። እነሱም ካቲኖን፣ ካቲን እና ታኒንሰ ናቸው። ካቲኖንና ካቲን በአወቃቀርም ሆነ በአስራር አንፊታሚን ተብሎ ከሚታወቀው ኬሚካል / መድሃኒት ጋር ተቀራራቢ ናቸው። ሆኖም አንፊታሚን በአሰራር ብርታት ከሁለቱም የጠነከር ሲሆን፤ ካቲኖን ደግሞ ከካቲን የበለጠ ነው። እነዚህ በጫት ውሰጥ ያሉ ሁለት ኪሚካሎች በይበልጥ በአእምሮ ውሰጥ በሚያደርጉት ለውጥና በሚያሰከትሉት ሰሜት በደንብ የታወቁ ሲሆን፤ ሊሎች የአካል ክፍሎቸንም የሚነኩ ናቸው። ታኒንሰ በአወቃቀርም ሆነ በአስራር ከካቲኖንና ካቲን በጣም የተለዩ ናቸው። አብዛኛውን በእነዚህ ሶሰት ንጥረነግሮች መኖር የተነሳ ጫት ቀጥሎ የተመለከቱተን ሁኔታዎች በስውነት ላይ እንደሚያመጣ ተመዝግቧል።

1. የአመለካከት ዝብርቅርቅነት: ጫት መቃም ከተጀመረ በአጭር ጊዜ ውሰጥ እንደአንፊታሚን (ግን ዝቅ ባለ ሁኒታ) ለአንጎል ንቃትን ይሰጣል። ለብዙ ቃሚዎች ይህ ሁኔታ የማሰብ፤ የመሰራትና የመናገር / የመወያየት “ችሎታን” ወይም ፍላጎትን ይጨምራል። በመጠኑም ቢሆን ይህ ድርጊት ደሰ በሚያስኝ ሰሜት የሚታጀብ ነው። ነገር ግን በተወስነ ተግባራዊ ጉዳይ ላይ ለማተኮር ጫት የአመለካከት ዝብርቅርቅነትን ብዙ ጊዜ ይፈጥራል። የሌሎች የተለያዩ ጫት ውሰጥ የሚገኙ ኪሚካሎች አሰተዋጻኦ የሚኖር ቢሆንም ካቲኖንና ካቲን አንጎል ላይ ለሚፈጠረው ሁኔታ ዋነኛ መንሲዎች ናቸው። ጫት መቃሙ ካበቃ በኋላም ቃሚው የመደበርና በቀላሉ የመናደድ ጸባይ ያንጸባርቃል። እንቅልፍ ያጣል፤ የምግቡም ፍላጎት ይቀንሳል። በሚቀጥለውም ቀን መፍዘዝ / መደበር ድካምና ሰንፍና ይጫጫነዋል። እነዚህን መጥፎ የሆኑ የጫት ልምዶችን ለማሰወግድና የእጹን መልካም – መሳይ አገልግሎቱን እንደገና ለማግኘት ቃሚው ጫት መውሰዱን ይቀጥላል። እያደር በይበልጥ ሱሰ ሰለሚያድርበት ቃሚው ጫቱን በይበልጥ ለመውስድ ይገደዳል / ይመርጣል። ሰለዚህ በየጊዚው ወደበለጠ ችግር ውሰጥ ይግባል ማለት ነው። ጫት በዚህ መልክ ለርጅም ጊዚ ሲወስድ አንፊታሚን እንደሚያመጣው ወደ ቅዠት የመስለ አመለካከት፤ ወደ በለጠ ድብርትነት፤ ተጠራጣሪነትና ወፈፊነት ያመራል። እነዚህ በጫት የሚመጡ ሁኒታዎች ቀድሞውኑ ተመሳሳይ የሆኑ የአእምሮ ችግሮች ባሉባቸው ቃሚዎች ላይ የሚብሱ ይሆናሉ።

2. የደም ብዛትንና የልብ መምታት መጨመር: በአእምሮ ላይ ከሚያሰከትለው ችግር በተጨማሪ ጫት የደም ብዛትንና የልብ መምታት መጨመርን እንደሚያመጣ ታውቃል። ጫት መቃሙ በቀጠለ ቁጥር እነዚህ ችግሮች እየባሱ በመምጣት ልብን በይበልጥ ሊጎዱ (ሊያቆሰሉ) ይችላሉ። እንደዚሁም አንዳንዴ ጫት በቃሚዎች አካል ውሰጥ የደም መፍስሰንና የአንጎል ደም የመዘዋወርን ችግሮች ያሰከትላል። እነዚህ ችግሮች አራሳቸውን የቻሉ አሰጊ ሁኔታዎችን ይፈጥራሉ። ለነዚህ የጤና ቀውሶት ካቲኖንና ካቲን ዋነኛ ሚና ይጫወታሉ። በዚህ አጋጣሚ መጠቀሰ ያለበት ጫት ለደም ብዛ ይረዳል ተብሎ በአንዳንዶች የሚታመነው ጉዳይ ሰህተት እንደሆነ ነው። እንደበፊቱ እነዚህ የተጠቀሱት የጫት ችግሮች ቀድሞውኑ ተመሳሳይ በሽታ ያለባቸውንና በእድሚ የጠኑ ቃሚዎችን በብዛት የሚያጠቁ ናቸው።

3. የአፍ ውሰጥችግርች: ከጥቂት ሁኔታዎች በሰተቀር ጫት በማላመጥ የሚወስድ በመሆኑ በአፍ ላይ የተውስኑ ችግርችን ያመጣል። ድድንና የሌላ የአፍ ክፍልን እንደመቁስል ያደርጋል። ጫት የአፍ ውሰጥ ካንስርም እንድሚያመጣ አንዳንድ መርጃዎች አሉ። ጫት ጥርሰን ማበለዙና ብሎም ማበላሽቱ በብዞች ቃሚዎች ላይ በግልጽ የሚታይ ነው። ከተዋጠም በኋላ የጨጓራ ህመምንና የአንጀት ድርቀትን ያሰከትላል። ታኒንሰ የተባሉት ንጥረነግሮች ለነዚህ ችግሮች ዋና ምክኒያቶች ናቸው። የሚፈጠሩት የሆድና የአንጀት ቀውሶች እላይ ከተጠቀስው የምግብ ፍላጎት መቀነሰ ጋር ሲደመሩ፤ ጫት በምግብ መጎዳት ምክኒያት የሚከስቱ ህመሞችን ያመጣል። ይህ ሲሆን ጫት ቃሚው የተላላፊ በሽታዎችን የመከላከል አቅሙ ይደክማል፤ ለተለያዩ ተላላፊ በሸታዎችም (ለምሳሌ እንደ ቲቢ ለመሳስሉ) ይጋለጣል። ጫት በጉበትም ላይ ችግር እንደሚያሰከትል መረጃዎች አሉ።

4. ሊሎች የጤና ችግርች: የግብረሰጋ ግንኙነትን አሰመልክቶ ጫት የወንዶችን ፍላጎት እንደሚቀንሰ ተጽፋል። ይህ ሁኔታ አንዳንድ ቃሚዎች በዚህ በኩል ካላቸው እምነት ውጪ ነው። ዘር ለመፍጠር የሚያገለግሉትን የወንድ ህዋሳት ብዛትና እንቅሰቃሲ / አስራር ጫት ይቀንሳል። በዚህ የተነሳ የማሰረገዝን ችሎታ የሚቀንሰ ነው። ካቲኖን ለዚህ ችግር ዋና መነሻ እንደሆነ ሳይንሳዊ መረጃዎች ያሳያሉ። የደም መዘዋወርንና ለሰዉነት አሰፋላጊ የሆኑ ምግቦችን በአካል ውሰጥ በመቀነሰ፤ በነፍስጡር ሲቶች ላይ የጽንሰ እድገትን ያቃውሳል። የሚወለዱት ልጆችም የቀጨጩ ይሆናሉ። በተጨማሪም የእናቶችን የጡት ወተት ጫት ይቀንሳል። ተጨማሪ ሳይንሳዊ ምርምሮች እንድሚያሳዩት በአንዳድ ቃሚዎች ላይ ጫት ሊሎች የተልያዩ የጤና ችግርችን ያሰከትላል። እንደምሳሌ የሳንባ ውሀ መቋጠርና የኩላሊት መታመም የሚጠቀሱ ናቸው። በጫት ላይ የሚደረገው ምርምር እሰከቀጠለ ድረስ ወደፊት የጫት ተጨማሪ ችግሮች ሊታወቁ እንደሚችሉ የሚገመት ነው።

ጫት እራሱ ከሚያመጣው የጤና ችግርች በተጨማሪ በብዙ ቃሚዎች የሚወስዱ ሊሎች ነገሮችም እንደዚሁ ጉዳት ይኖራቸዋል። ከነዚህ መካከል የአልኮል መጠጥና ሲጋራ ዋነኛዎቹ ናቸው። የአልኮን መጠጥ ከጫት መቃም በኋላ የሚወሰድ ሲሆን ሲጋራ ከመጀማሪያው አንሰቶ የሚወሰድ ነው። መጠጥ አንጎል ላይ ባለው ጥቃት እራሰን በማሳት ከሰህተት ያሚጥል ነው። ብዙ ጫት የሚቅሙ ስዎች ለዚህ ችግር የመጋለጥ እድል አላቸው። ከመጠጥ በኋላ ልቅ በሆነ መንገድ የግብረሰጋ ገኑኝነት ለሚያደርጉ በይበልጥ ለኢች.አይ.ቪ. የሚጋለጡ ለመሆናቸው መረጃዎች አሉ። መጠጥ ተደጋግሞ ሲወስድም በራሱ እንደጉበት መበላሽትን፤ የደም ብዛትን፤ የጨጓራ ህመምንና መንቀጥቅጥን የመሳሰሉ ችግሮችን ያሰከትላል። ሲጋራም እንደዚሁ በርከት ያሉ የጤና ችግሮቸን የሚያሰከትል ሲሆን በቀዳሚነት የሳንባና የልብ በሽታዎች መነሳት ያለባቸው ናቸው። ከጫት ጋር የእነዚህ የሁለት ነገርች ችግር መጨመር ምን ያሀል በቃሚዎች ላይ የጤንነት መጓደል እንደሚኖር መገመት አሰቸጋሪ አይሆንም። ቃሚዎች ከጫት ጋር ሰኳር ወይም ሰኳር – ነክ የሆኑ ነገሮችንም አብረው ይወሰዳሉ። ሰኳር በአፍ ውሰጥ ተይዞ ሲቆይ ለጥርሰ ጤንነት ጥሩ አይደለም። ከተዋጠም በኋላ የደምን የሰኳር መጠን የጨምራል፡ ይህ ሁኔታ የሰኳር በሽታ ላለባቸው በይበልጥ ጎጂ ይሆናል።

ጫት በሚወስድበት ጊዜ አንዳንድ መድሓኒቶች አብረው ከተውሰዱ በመካከላቸው ግጭት ሊፈጠር ይችላል። ለምሳሌ ያህል ጫት የአንፒሰሊንና የአሞክሰሊን አግልግሎት ሊቀንሰ የሚችል ሲሆን የፍራዞሊደንና የእንቅርት መድሃኒቶችን የሰራ ሀይል ይጨምራል። ሰለዚህ እነዚህም ሆኑ ሌሎች መድሃኒቶች የሚውሰዱ ከሆን፤ ቃሚዎችም ሆኑ የጤና ባለሞያዎች መድሃኒቶቹ ከጫት ጋር ሊኖራቸው የሚችለዉን ግጭት / ግንኙነት በማወቅ ተገቢውን እርምጃ መውስድ የገባቸዋል።

ጤንነትን አሰመልክቶ ጫት ለአንዳንድ በሽታዎች እንደሚጠቅም የሚያምኑ ቃሚዎች አሉ። በዚህ መስረት ብዙ ቃሚዎች ጫት ለደም ብዛት፤ ለራሰ በሽታ፤ ለሆድ በሽታ፤ ላባለዘር በሽታ፤ ለሰኳር በሽታ እና ለግብረሰጋ ግኑኝነት ችግር ይጠቅማል ይላሉ። እነዚህ አሰተሳሰቦች ካለመረጋግጣቸውም በላይ ከላይ እንደተገልጸው አንዳንዶቹ ከሳይንሰ መረጃዎች ተቃራኒና ጭራሽ ጎጂዎች ናቸው። ሰለሆነም ሰለ ጫት የሚኖሩ አንዳንድ ጭፍን እምነቶች ሊታስብባቸውንና ጥንቃቄ ሊደረግባቸው የሚገባ ነው።

ለማጠቃለል ያህል ጫት በተለያዩ መንገዶች ለጤንነት ጎጂ መሆኑን የሚያመለክቱ ሳይንሳዊ መረጃዎች እንዳሉ መገንዘብ ያሻል። ለወደፊቱም ቢሆን የበለጠ መረጃዎች ሊቀርቡ ይችላሉ። በነዚህ መረጃዎች መስረት አሰፈላጊው ጥንቃቂ መወሰድ አለበት። የማረጋገጫ መረጃዎች እሰከሌሉ ድረሰ ጫት አይጎዳም ወይም ይጠቅማል ብሎ መጠቀሙ የሚጎዳ ይሆናል። በሱሰ ለተጠመደ ቃሚ ጫትን መተው አሰቸጋሪ ቢሆንም ፡ ጥረት ከተደረገ ማቆም የሚቻል ነው። ጫት መቃሙ ከተተወ በርከት ያሉት ጎጂ ጸባዮቹ ሊሰተካከሉ / ሊቀሩ የሚችሉ ናቸው። ጭራሹኑ ከቁጥጥር ውጪ ካልሆነ በሰተቀር ጤንነትም እንደዚሁ ሊመለሰ ይችላል። ቃሚው ይህንን በራሱ ለማድረግ የማይቻል ከሆነ፤ በጤና ባለሞያዎች እርዳታ ከችግሩ መላቀቅና ከዚያም እራሱን መጠበቅ የሚቻል ነው። በጫት የተጠመዱ ሁሉ እነዚሀን አማራጮች እንዲሞክሩ ይመከራሉ። በተጨማሪም በጤንነት ከመጎዳት ባሻገር የጫት ሱሰ ያለባቸው ቃሚዎች ህጋዊ በሆነ መንገድ ወደ አንዳንድ የውጪ አገሮች ለመጓዝ የሚያሰችሉ ፍቃዶችን ማግኘት ምናልባት ሊቸገሩ እንደሚችሉ የሚያመለክቱ ፍንጮች ብቅ ማለታቸውን ማወቁ ሊጠቅም ይችላል።

Source: http://www.mahderetena.com
Comment
There are no comments made yet.
Accepted Answer Pending Moderation
0
Votes
Undo
Asnake Gebeyehu wrote:

Chat or khat I don't know how it is written, but dangerous leaf. In my university there are many students who eat chat and are addicted. We call them jezbawoch because they can not activly participate if the didnot get chat.
Comment
There are no comments made yet.
  1. more than a month ago
  2. Life Skills
  3. # 1
Accepted Answer Pending Moderation
1
Votes
Undo
Chat or khat I don't know how it is written, but dangerous leaf. In my university there are many students who eat chat and are addicted. We call them jezbawoch because they can not activly participate if the didnot get chat. I say it is a big problem of university students. I think leders must work to prevent addiction.
Comment
There are no comments made yet.
  1. more than a month ago
  2. Life Skills
  3. # 2
  • Page :
  • 1


There are no replies made for this post yet.
Be one of the first to reply to this post!