1. Abel Abebe
  2. Life Skills
  3. Wednesday, 12 July 2017
ስኬት ማለት ምንድነዉ?
ክፍል ፩
ስኬትን በምንድነው የምንገልፀዉ? ልጅ እያለው ትዝ የሚለኝ ሁልጊዜ ቤታችን እንግዳ ሲመጣ ቤተሰቦቼ ሒድና ለጋሽ እከሌ የትምህርት ወጤትህን አሳየው እባላለሁ እኔም ብርርርር እልና ይዤ መጥቼ አሳያለሁ ከዛ "ጎሽ የኔ ልጅ እንዲህ ነው አንበሳዬ ወደፊት ዶክተር ነው የምትሆነው" እባላለሁ ያዙልኝ እንግዲ የስኬት የመጀመሪያው ጥያቄ ወይም መንገዱን የሚያሳያችሁ እዚህ ጋር ነው "ዶክተር ነው የምትሆነው ?!" እንደኔ ዓይነቱ መርፌ የሚፈራ ልጅ ፣ ነጭ ጋወን ለብሶ ሠፈር ውስጥ የሚንቀሳቀስ ሲያይ እየሮጠ ከቤቱ አልጋ ስር የሚደበቅ ይሄ እርግማን እንጂ ምርቃት አይደለም። ከዛ ደሞ ቀጣዪ ጥያቄ ይመጣል፣ "ማሙሽዬ ስታድግ ምን መሆን ነው የምትፈልገው ?" ወታደር እል ነበር ዕድሜ በዛ ዘመን ቅዳሜ ቅዳሜ ለሚታየው የሳምንቱ ታላቅ ፊልም። በቃ ይህን ጥያቄ ጎረቤት ይጠይቅሀል፣ ዘመድ ይጠይቅሀል፣ የሰፈር ጎረምሳ ኩርኩም አቅምሶ ከላከክ በኋላ ይጠይቅሀል፣ ከሁሉም የሚገርመኝ ደግሞ ትምህርት ቤት አስተማሪ ሲጠይቁኝ ነው ስራው አንተ ብርቱ እና ጠንካራ የሆንክበትን ዝንባሌ ለይቶ አውጥቶ እሱን እንድታጎለብት መንገድ ማሳየት ሲገባው አይንህን አውሮ አንተኑ መንገድ አሳየኝ ይልሃል። ለነገሩ አይፈረድበትም ይሄኔ እሱም በልጅነቱ ተጠይቆ ፓይለት እሆናለው ብሎ ይሆናል አስተማሪ የሆነው። ይህን ሁሉ የቀባጠርኩበት ምክንያት በእኛ ህብረተሰብ አናኗር ዘይቤ ስኬት አንድ እና አንዳጅ ነው። መማር፣ዩኒቨርሲቲ መግባት፣ ዲግሪ መጫን (ቢቻል በህክምና ሳይንስ ዶክተር መሆን ወይም በምህንድስና ሳይንስ መሐንዲስ መሆን በነዚ ካልተቻለካግን በሌላ በማንኛውም ዘርፍ)፣ ከዛ ሥራ መያዝ (አሱም ከተገኘ ወይም ጥሩ ዘመድ ካሎት) ከዛ በቃ ወር ከወር ፔይሮል አሳደው ፈርመው ደሞዝ መብላት። ለኛ ህብረተሰብ ይሄ በቃ አሸወይና ነው ።
ለናንተ በህይወቶ ስኬታማ ነኝ የሚሉት ምን ሲያሳኩ ነው? በክፍል ፪ እስክንገናኝ ያመቻቹ
Comment
There are no comments made yet.
Accepted Answer Pending Moderation
0
Votes
Undo
Abel Abebe wrote:

  1. more than a month ago
  2. Life Skills
  3. # 1

  3. # 2
  • Page :
  • 1

There are no replies made for this post yet.
Be one of the first to reply to this post!