[u]ረመጥ[/u]
አለም የኤች. ኣይ. ቪ ኤድስ በሽታን ካስተናገደች እነሆ ሦስት አስርተ ዓመታትን አስቆጥራለች። ዛሬ ዛሬ ወደ 35 ሚሊዮን የሚጠጉት የዓለማችን ሰዎች ከቫይረሱ ጋር ይኖራሉ። ከነዚህም ዉስጥ ከሰሃራ በታች የሚገኙት የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳሉ። በሽታው በፕላኔታችን ከተከሰተ ጀምሮ ስርጭቱን ለመቀነስ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ዘርፈ ብዙ ስራዎች ሲከናወኑ ቆይቷል። ለግንዛቤ ማስጨበጭያ፤ ለስርጭቱ መግችያ ብለው የተለያዩ የመንግስትም ሆነ የግል በጎ አድራጊ ድርጅቶች የትየለሌ መዋለ ንዋያቸዉን አፍሰዋሉ ሚድያዎች የአየር ሰዓታቸውን ሰውተዋሉ ፓምፍሌቶችና ብሮሸሮች ተበትነዋሉ። አዎን የአውራ ጎዳናዎች ቢልቦርዶች ሳይቀሩ ስለ ኤድስ በሽታ ብዙ ብዙ ብለዋሉ። ሆኖም ግን ምንም እንኳን ለበሽታው የተዳረጉትን ሰዎች የጤናቸውን ሁኔታ ማሻሻል ብቻልም ዛሬም መፈወሻ መድሃኒትም ሆነ መከላከያ ክትባት ማግኘት አልተቻለም። አለማችንም በበሽታው ሳብያ በርካታ የነገ ሀገር ተረካቢ ህጻናትን እና አፍላ ወጣቶችን ተነጥቃለች። አዎ!የለጋ ታዳጊዎችን ወላጆች አጥታ ከአፈር ቀብራቸዋለች። እናም ኤች. ኣይ. ቪ ኤድስ አሁንም የህይወት ስጋት ሆኖ ቀጥሏል።
የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እንደ መሆኔ የፅሁፌን ትኩረት በሽታው በዩኒቨርሲቲዎች ያለዉን ሽፋን ለመዳሰስ እሞክራለው። ሀገራችን ከ 30 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች ባለቤት ናት። እነኝህ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሀገር ተረካቢ ምሁራንን አስመርቀው ወደ መሀበረሰቡ ያሰማራሉ። ግና ይህ በንዲህ እያለ የነገው የሀገሪቱ ተስፋ የሆነው ወጣቱ የልማት ሀይልን ረመጡ ኤች. ኣይ. ቪ ኤድስ እያሳደደው ይገኛል።
በተለያዩ ግዜያት በአዲስ አበባ߹ ሀዋሳ ጎንደር ጅማ ሚዛን ቴፒ መደ ወላቡ እና መሰል ዩኒቨርሲቲዎች የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የበሽታው ስርጭት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ቀላል እንዳልሆነ ያሳያሉ። ታድያ ዩኒቨርሲቲዎች የምሁራን መፍለቅያ ሆነው ሳለ የኤች. ኣይ. ቪ ኤድስ ስርጭት እንዴት ከፍተኛ ሊሆን ቻለ? ይህ የሁሉም ሰው ጥያቄ ነው። ኤድስ ምሁር ማይም ህብታም ድሃ ትንሽ ትልቅ አይልም በመንገዱ የመጣውን ሁላ ያጠቃል። በጥናቶቹ የስርጭቱ መንስኤዎች ተብለው ከተጠቀሱት አንኳሮቹ የሚከተሉት ናቸው። ስለ በሽታው በቂ ግንዛቤ ማጣት߹ የጓደኛ(የአቻ)ግፊት߹ የኢኮኖሚ ችግር߹ለተለያዩ ሱሶች (መጠጥ߹ ጫት߹አደንዛዥ ዕፅ)መጋለጥ በተጨማሪም pornographic ፊልሞችን መመልከት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
ታድያ ይህን የነገን ሀገር ተረካቢ ትውልድን የበሽታው ሰለባ እንዳያሆን ዛሬም ከምንም ጊዜ በላይ ወደ በሽታው ማዳረሽያ የሆኑትን ከላይ የተጠቀሱትንና ያልተጠቀሱትን መንገዶች ለመቀነስ ከፍተኛ ርብርብ ያስፈልጋል። ትልቁ እና ዋንኛው የባህሪ ለውጥ(Behavioral change)ነው። አዎ!ትውልድ እንዲድን ስለበሽታው ግንዛቤ ከትውልዱ አንደበት ሰርጾ ሊገባ ይገባል። በተለይ ዩኒቨርሲቲዎች ከፕሬዝዳንት እስከ ጥበቃ ፖሊስ ሁሉም በመተባበር ”የበግ ተራ“ ስፍራዎችን በማስወገድ፤ ለተለያዩ ሱሶች የተዳረጉትን ተማሪዎች የምክር አገልግሎት በመስጠት፤ በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ለስነ_ተዋልዶ ችግሮች የሚዳረጉትን ሴት ተማሪዎች የሚረዱበትን መንገድ በማመቻቸት፤ እንዲሁም የpornography ድረ_ገጾችን በማገድ (block) እና ሌሎች መንገዶችን በመጠቀም ስርጭቱን እንግታ ባይ ነኝ።
በመጨረሺያ ከሁለትና ሶስት ዓመታት ወዲህ በተለይ በሀገራችን ኢትዮጵያ ስለበሽታው ከሚደረገው ርብርብ ትንሽ መዘናጋት ይንፀባረቃል። ለምሳሌ ድሮ ድሮ በቀን ሶስት አራቴ በሚድያ የሚዘከረው ኤች. ኣይ. ቪ ኤድስ በሽታ ዛሬ ላይ አንዴም ሳይወሳ የሚያልፍባቸው ቀናቶች ጥቂት አይደሉም። ይህም ሊሆን የቻለው ከባለፉት 10 ዓመታት ወዲህ የበሽታውን ስርጭት አመርቂ በሆነ መልኩ መቆጣጠር ስለተቻለ እንደሆነ ይነገራል። ግና አሁንም በሽታው እንደ ረመጥ ተዳፈነ እንጂ አልተወገደምና ሁሉም የሚመለከተው አካል ስርጭቱን ለመግታት በተጠናከረ መልኩ የድርሻችንን እንወጣ እያልኩ ፅሁፌን በዚሁ አበቃለው።
የጋራ ርብርብ ለነገው ጤናማ ሀገር ተረካቢ ትውልድ!
ተፈፀመ
በተማሪ ዩሱፍ ገብሬ_ ሰኔ 1 2009 (From Jimma University Department of Medical Doctorate) phone no. 0937331381
- Yusuf Gebre
- ዳሰሳዊ ፅሁፎች / Featured Articles
- Thursday, 08 June 2017
Comment
There are no comments made yet.
There are no replies made for this post yet.
Be one of the first to reply to this post!
Be one of the first to reply to this post!