1. Ahmed Ebrahim
  2. ዳሰሳዊ ፅሁፎች / Featured Articles
  3. Wednesday, 17 May 2017
በመጀመሪያ ሰላም ክብር ፍቅር ጤና ለተማሪ ኔት አባላትና ለ DKT ethiopia አስተባባሪዎች ይህን እላለሁ፡፡
በተለያዩ የአለም አህጉራትና በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያየ ጊዜ የተለያየ አመለካከት አስተሳሰብ ቀለምና ቁመት ውፍረትና ቅጥነት ያለን ሰዎች ምድርን አልቅሰን እንቀላቀላለን….ደግሞም የምድርን ህይዎት ኑሮን አጣጥመን በልተን ጠጥጠን ተጫውተን ሳንጠግብ እንደጀመርናት ሳንጨርሳት እንደቀመስናት ሳንጠግባት በተለያዩ ምክንያቶች ይችን ምድር ወደን ሳይሆን ተገደን እረቃናችንን አልቅሰን እንደመጣን እርቃናችንን ምንም ሳን|ይዝ እንድንሄድ እንገደዳለን፡፡ወጣትነታችንን ሳንጠቀምበት ሳናጌጥበት ሳንደሰትበት ካሰብነው እንዳደርስ ከሚከለክሉ የመንገድ ዳር እንቅፋቶችና ወጥመዶች መካከል ብዙዎቹን እያወቅን እንዳላወቅን የምንፈፅማቸው ድርጊቶች ናቸው፡፡ወጣት ማለት ተጫውቶ ሩጦ ስቆ ያልጠገበ ረጅም የስኬት መንገድ ለመጓዝ ያሰበ የስንቅ መንገደኛ ማለት ሲሆን ያንን ረጅሙን የሕይወት ግብ ካቀድነውና ካሰብነው እንዳንደርስ ብዙ መሰናክሎችና እንቅፋቶች በየ ሂዎት መስመራችን እናገኛለን ፡፡ በተለይ እኛ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተለያየዩ መርዞች ተመርዘን መጀመሪያ ግቢ ስንገባ ቤተሰብ የጣለብንን አደራ ወደጎን በመተው በአግባቡ ሳንወጣ ከንቱ ሆነን የምንቀር ብዙዎች መሆናችን አይዘነጋም ፡፡ ባሁኑ ሰአት በሀገራችን የተዳፈነ እሳት መስሎ እያለ እንደሌለ በመምሰል ወገኖቻችንን በመግደል በሰፊው እየተዛመተ የሚገኘው ያ የሳት ረመጥ መድሀኒት በሀኪሞች ያልተገኘለት ግን እኛ እራሳችንን ከጠበቅን ሀኪሞች ከሚቀምሙት መድሀኒት ይልቅ እኛ እራሳችን በሰውነታችን ውስጥ ተጠምዶ ሳይሆን ፈንድቶ እያቃጠለ አካላዊና ማህበረሰባዊ ስነልቦናዊ ጉዳትን በማጎናፀፍ አስገድዶ ውስጥ ውስጣችንን ለሚያቃጥለው ወጣትነትን እንደበረዶ ለሚያቀዘቅዘው ወጣትነትን ፅሀይ እንበዛበት ፅጌሬዳ አበባ ለሚያጠወልገውና ለሚያደርቀው የ HIV/ADS በሽታ መስፋፋት በዩኒቨርስቲ ውስጥ ዋና ዋና ምክንያቶች በኔ አስተሳሰብ የሚከተሉት ናቸው፡-
1/ ራስን አለመውደድና ለራሳችን የምንሰጠው ግምትና ክብር የወረደ በመሆኑ ነው ምክንያቱም ለህይወታችን ክብር ቢኖረንማ ራሳችንን ካደጋ እንጠብቅ ነበር፡፡
2/ በ አቻ ግፊት አማካኝነት የሚመጣ ያለፍላጎት ሳይተዋወቁ ሳይግባቡ ተቃራኒ ፆታ መያዝ … …
3/ የ 7ኛ አመት ተማሪ ፍሬሽ ተማሪ ይለክፋል እሱ በሽተኛ ነው እሷ ስለሱ ምንም አታውቅም ጓደኛ መያዝ ብርቅ መስሎ ስለሚታያት; እሷም ተመርቃ እሰክትወጣ ለ3 ወይም ለ 5 ወይም ለ7 አመት የተሰጠችውን ስጦታ እንደ ደህና ነጋዴ ስታከፋፍል ትኖራለች::
4 / በተለያዩ ሰአቶች ማነቱን/ማንነቷን ከማናውቀው ሰው ጋር ሳይመረመሩና ኮንዶም ሳይጠቀሙ የግብረስጋ ግንኙነት መፈፀም..
5/ በሽተኛው ራሱን በመደበቅ ጤነኛ መስሎ የተለያዩ ሴቶችን በመልከፍ…በተለይ …ወንዶች… እህቶቻችን ላይ የምንፈፅማቸው…ድርጊቶች…. የሴቶች… መታመም .የሚያሥደስተን ያስመስልብናል፡፡
6/ የተለያዩ ድብቅ ቦታዎች በግ ተራንና ግትር ተራን ምክንያጥ በማድረግ ጨለማን ተገን አድርጎ በሚፈፀም መተሻሸት በስሜት አስገዳጅነት የሚፈፀም ልቅ የሆነ ግብረ ስጋ ግንኙነት …..
7/ ብር አጣን አጠረን በሚል ምክንያት ሴቶች ሹገር ዳድ ወንዶች ደግሞ ሹገር ማሚ ….
8/ ዶርም ላይ ስለታም ነገሮችንና ጭሳጭሶችን በጋራ መጠቀም……..
9/ ከመጠን በላይ በመጠጣትና በመስከር በየቀኑ ከተለያዩ ሴቶች/ወንዶች/ ጋር የሚደረግ የግብስጋ ግንኙነት….
10/ የተቃራኒ ፆታዎች ባንድ ለመወሰን እርስ በረስ አለመተማመን
11/ በተፈጥሮ ወንዶች በፈጣጣው ሲዋሹ ሴቶች ደግሞ ተደብቀው ስለሚዋሹ ነው፡፡
12/ ብር እየተከፈላቸው በሚሰሩ ደላሎች አማካኝነት የሚመጣ የሚደረግ ……የሥጋ…ድለላ……..
13/ ከግቢ በመውጣት ከተለያዩ ጭፈራ ቤቶች በር……………..እራስን ለመሸጥ በሚደረግ የሥጋ ችርቻሮ የንግድ ማእከል
………..አቤት የሥጋው ገብያ…………
በ 1 ቀን ምሽት ከስንተ ሰው ጋር
በ 1 ሳምንት ምሽት ከስንተ ሰው ጋር
በ ወር ቀን ምሽት ከስንተ ሰው ጋር
በ 1 አመት ምሽት ከስንተ ሰው ጋር
በ 3 አመት ምሽት ከስንተ ሰው ጋር
በ 5 አመት ምሽት ከስንተ ሰው ጋር
በ 7 አመት ምሽት ከስንተ ሰው ጋር
ፈጣሪ ይጠብቀን!!!!!!!!!!!!!!
እንኳን ለፈፀመው ለሚያሥበው ሰው ይዘገንናል!!!!!!!
የሴቶች አለባበስ የወንዶችን ስሜት ለመቀስቀስ የሚሰራ ታላቅ ፕሮሞሽን
----›› ወንዱ ሙሉ ሱሪ ለበሶ ጫማውን ተጫምቶ ሲወጣ ሰቷ ደግሞ በፓንትና ሚኒስከርት ወይም ፓነት በሌለው ሚኒስከርት…… እርቃኗን››››››››››››
ዋነኛው የበሽታ መስፋፊያ መንገድ ግን ባህላችንን በመጣል የምናደርገው መሽለጥለጥ ልብስ ሳይታጣ እርቃናችንን መሄድ ወጣቶችን ለዝሙት /ላልተፈለገ የስሜት መገፋፋት /መነሳሳት/ የምናደርገው /የምንሰራው /ፕሮሞሽን እና
በሀገራችን የግሉን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚታገል እንጅ የወገን ጉዳት እና እልቂት የማይቆረቁረው ፊደል የቆጠርን እንጅ አስተሳሰባችን ያልተቀየረ ተምረን ያልተማርን ባስተሳሰብ የወረድን ሰዎች በመብዛታችን ነው፡፡
ለችግርና ለስቃይ ምክንያት በመሆን ሳይሆን ችግር ላይ ያሉትን ከችግር በማውጣትና እንዳይገቡ በማድረግ ወገናዊ ግደታችንን እንወጣ!!!!!!
ሰላምና ጤና እድገት ብልግና ለተማሪ ኔት አባላትና ለኢትዮጵያ ሀገራችን ይሁን!!!
Comment
There are no comments made yet.


There are no replies made for this post yet.
Be one of the first to reply to this post!