1. Shimeles Gebeyehu
  2. Life Skills
  3. Wednesday, 11 May 2016
ውድ የ TemariNet አባላት,
ወቅቱ የፈተና ነው ፡፡ እናም ውጥረቱ ከፍተኛ ነው፡፡ የፈተና ወረቀት ይዞ ለሚመጣው ማንኛውንም ፈተና በመዘጋጀት ላይ እንደሆናችው ይሰማናል፡፡ ፈተና በቀሪው የሕይወት ምዕራፋችን ላይ መወሰን እንደሚችል ማወቃችን የፈተና ወቅትን ይበልጥ አሰቃቂ ያደርገዋል፡፡ በርካታ ተማሪዎች በዚህ ጊዜ ላብ ላብ ይላቸዋል፤ መሸበርም ይጀምራሉ፡፡ በፈተና ወቅት የሚያስመልሳቸው፤ የሚያንዘፈዝፋቸው እንዲሁም ዝለው የሚወድቁም ተማሪዎች አሉ፡፡ በፈተና ወቅት ምን አዝናኝ ገጠመኝ አልዎት? እኔ ያነበብኩትን ላጋራቹ፡፡
የሐሳብ ፈተና ላይ ነው፡፡ በድንገት ተማሪዎች በፈተና ወቅት ያልተለመደ ድምጽ ያሰማሉ፡፡ ጩኸት፣ሳቅ፣ ኳኳታ፡፡ መንስዔው በዴስኮች መካከል የሚሄድ አንድ የአይጥ ቤተሰብ ነበር፡፡ ፈታኙ ሁሉም ተማሪዎች ዝም እንዲሉ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ሀሳባቸውን ሰብስበው ወደ ፈተናው እንዲያተኩሩ መመሪያ አዘል ምክር ሰጠ፡፡ ለጊዜው የተማሪዎቹ ግርግር ሰከን አለ፡፡ ነገር ግን በየ 20 ደቂቃው የአንድ ሰው እግር በአይጥ ስለሚደፈር ጩኸት፣ሳቅ፣ ኳኳታ ይቀጥላል፡፡ በመጨረሻም ፈታኙ ተማሪዎቹ የቀራቸውን ጊዜ ለመንገር ሲዘጋጅ የእርሱ አግር በአይጥ ይዳበሳል፡፡ እሱም በታላቅ ጩኸት "አሁን 10 አይጦች ቀርቷችኋል" በማለት የቀሪ ሰዓት ማሳሰቢያውን ለተማሪዎቹ አደረሰ፡፡ የተማሪዎቹ ጩኸት፣ሳቅ፣ ኳኳታ እንደገና ገነፈለ፡፡

የእርስዎን የፈተና ወቅት ገጠመኝ ያጋሩን!

መልካም የፈተና ሰሞን ይሁንላችው!

http://i.telegraph.co.uk/multimedia/archive/03370/Exam2-Getty_3370351b.jpg
Comment
There are no comments made yet.


There are no replies made for this post yet.
Be one of the first to reply to this post!