1. Negusu Ferede
  2. ግጥሞች / Poems
  3. Sunday, 23 April 2017
ከዚህ እኛ ሰፈር የነበሩት ልጆች፣
ቆነጃጅት ሴቶች የትናንቱ ወርቆች፣
ውበታቸው ልዩ ሁሉንም አሳቾች፣
ዛሬ ግን ጠፍተዋል መቃብር ወረዱ፣
ቤታቸው ተዘጋ ውበታቸው ጠፋ፣
ስማቸው ተረሳ ሀብታቸው ረገፈ ፣
አጥንታቸው ምድርን ክፉኛ መረዘ፣
ምድርም አለቀሰች እንባዋን ጨመረች፣
በወጣቶች አጥንት ጎኗን እየተወጋች።
እነዚያ ወጣቶች አትሌት የነበሩት፣
ሀገራቸውንም ከፍ አርገው ያስጠሩት፣
በራሳቸው ድካም በአለም የታወቁት፣
ለሀገር አለኝታ ኩራትና ተስፋ መከታ የሆኑት፣
በአለም መድረክ ላይ ደምቀው የነበሩት፣
ዛሬ ላይ መቼ አሉ የትስ ተሸሸጉ፣
እንዴት በአንድ ጀንበር ታየተው ለምን ጠፋ።
ብየ ብጠይቃት ሀገሬን በእርጋታ፣
የሉም ተጥለዋል ከመቃብር ቦታ፣
ዝናቸው መሬት ውስጥ በአፈር ተደብቋል፣
ክብራቸው መንምኖ ድንጋይ ተጭኖታል፣
መሬትም አዝናለች ከልቧ አልቅሳለች፣
በወጣቶች አጥንት ጓኖን ተወግታለች።
ብላ ስትነግረኝ በሀዘን ውስጥ ሆና፣
እኔም ቀጠልኩላት ልጠይቃት ገና፣
እነዚያስ የታሉ ታላላቅ ምሁራን፣
በእውቀት የመጠቁ ሳይንስን ያወቁ፣
አገርን ለመምራት ለእጩነት የበቁ፣
ታሪክን መርምረው ለአሁን ያሳወቁ፣
ለወጣቱ ትውልድ ተስፋ የነበሩ፣
እነሱስ የት ገቡ መቼ አሉ ከወንበሩ፣
ክብራቸውስ የት አል ትንፋሻቸው ጠፍቷል፣
የጀመሩት ስራ ከምን ላይ አቁሟል፣
ንገሪኝ እማማ ዝናቸው ቀዝቅዟል፣
እያልኩ ስጠይቃት ግራ ይጋባታል፣
አንገቷን ዘቅዝቃ ታናግረኛለች፣
የሉም አልኩኝ የሉም መቃብር ወርደዋል፣
ጥበብን ደብቀው ከአፈር ወድቀዋል፣
ስጋቸው ለጉንዳን ምሳና ራት ሆኗል፣
በመቃብር ጎጆ አርፈው ተኝተዋል፣
እውቀታቸው ባዶ ጭቃ ቅብ ሆነዋል፣
እያለች ስትነግረኝ እኔም ተናድጀ ደግሜ ጠየኳት።
ይኸ ሁሉ ሲሆን እንዴት ዝም አልሻቸው፣
ለምን አትገዝችም ማዕቀብ አትጥይም፣
ስለ ሞት አጥብቀሽ ለምን አልነገርሽም፣
እንዴት ሰው ይሞታል በወጣትነቱ፣
ገና በለጋ እድሜው ሳይባል አባ አንቱ፣
እንቡጥ ላይ እያለ ሳያብብ ከልቡ
ንገሪኝ ሀገሬ አስረጂኝ አምልተሽ፣
ማነው አሳዳጅሽ እንዲህ የከፋብሽ፣
ማወቅን እሻለው እማየ እንዳይከፋሽ፣
በማለት ስጠይቅ እሽታ ሰጠችኝ፣
አዎ....ጎስቁያለው፣
በሀዘን ከስየ በእንባ ታጥቢያለው፣
ውስጤ ባዶ ቀርቶ ብቸኛ ሆኛለው፣
አይኖቸ ጠፍተዋል መንገድ አጥቻለው፣
በብርሀን ሳለው መራመድ ትቻለው፣
የጠላቴን ክፋት ሁሌ እናገራለው።
ሞት ነው የኔ ጠላት ልጆቸን ያሳጣኝ፣
ህፃናትን ከእናት ያስተዛዘበብኝ፣
ገና አፋን ሳይፈታ ያነጣጠለብኝ፣
ጡት ጠብቶ ሳይጨርስ አፈር ያገባብኝ፣
ይዘል የነበረዉ እንደ ጥጃ አምቦሳ፣
እንዲሕ ኩርምት ብሎ ተሰብሮ እንደጣሳ፣
ማየቱ ወጣትን በመንገድ ተኝቶ፣
ሕሊናን ይጎዳል ይገላል አቃዥቶ::
የቀርቀኃ-ጥራር መስሎ ደረቱ ላይ፣
አጥንቱ ተቆጥሮ ጂማቱ እስከሚታይ፣
ምድር-አለቀሠች ምርርር ብላ እንደ ሠው፣
ከርሠ-ምድር-ጎኗንአጥንት እየወጋዉ::
አዲስ ሆኖ ለእርሷ ለገላዋ እንግዳ፣
አፅምን መቀበል በመቃብር-ጓዳ፣
ምድር-አለቀሠች ስቅስቅ ብላ እንደሠዉ፣
ሆዷ እስኪፈነዳ፣
የወጣቶች አጥንት ጎናን እየወጋዉ::
የምሬት ደብዳቤ የኃዘን እምባዋ፣
አልደርሥላት ብሎ እርሷን ከፈጠረ ከልዑል ጌታዋ፣
ግራ-ግብት አላት! አጥንት ብቻ ሆነ ደሳሳ ጎጆዋ።
እያለች ስትነግረኝ ግራ ገባኝና ጥያቄ ጨመርኳት፣
ቆይ ቆይ ግን እናቴ ውዲቷ ሀገሬ፣
እንዲህ ያሳዘነሽ ምድርን ያስለቀሰ፣
ወጣት ሽማግሌ ህፃን የጨረሰ፣
ሁሉንም መቃብር አፈር ያለበሰ፣
ወታደር ኢንጅነር ተማሪ ነጋዴ ሁሉንም
ያሳጣሽ፣
ዶክተር መምህራን ገበሬ መቃብር የጣለ፣
ህፃንን ያለ እናት ደካማን ያለ አጋዥ ለይቶ ያስቀረ፣
ንገሪኝ እማማ ንገሪኝ ጠላትሽን በደንብ ልወቀው።
ቀና ብየ ሳያት በጣም እያነባች እያሰቀሰቀች፣
እንባዋን እንደ ጅረት በፊቷ እያወጣች፣
ትንፋሽ እያጠራት ጎኗን እየራቃት፣
ፊቷ በጣም ጠቁሮ አጥንቷ ተቆጥሮ፣
ጠላቴ እማ ልጄ HIV AIDS ነው።
አዎ እሡ ነው ጠላቴ በጣም አሳዳጄ፣
ምድርን ያስለቀሰ በወጣቶች አጥንት ጓኗንም ያስወጋ፣
ህፃንን ያለ እናት በባዶው ያስቀረ፣
እናም እኔ እናትህ አሁን ዝም አልልም፣
ወገቤን አጥብቄ ቆርጬ እነሳለው፣
ስለ AIDS ክፋት ደግሜ ደግሜ ደግሜ እነግራለው።
አዎ ዝም አልልም እመሰክራለው፣
የመሬትን ልቅሶ እነግራለቸዋለው፣
የመቃብርን ምሬት አስተምራቸዋለው፣
አንሶላ አትጋፈፍ ከዝሙት ራቁ፣
አንድ ላንድ ተወሰኑ ብሎም ተጠቀሙ፣
አልፎም ተመርመሩ ራሳችሁን እወቁ፣
ብየ እነግራቸዋለው አስተምራቸዋለው፣
ብላ ነገረችኝ ስለ AIDS ክፋት አስተዋወቀችኝ።
Comment
There are no comments made yet.


There are no replies made for this post yet.
Be one of the first to reply to this post!